ለህጻናት ማቆያ ሞግዚቶች እና ባለሙያዎች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተሰጠ

ለእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የህጻናት ማቆያ ሞግዚቶች፣ ነርሶች፣ ባለሙያዎች እና የጽዳት ባለሙያዎች አጠቃላይ የህጻናት አያያዝ እና እንክብካቤ ላይ ያተኮረ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተሠጥቷል፡፡

ስልጠናውን የከፈቱት የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ባንቻለም ካሴ የስልጠናው ዓላማ የህጻናት ማቆያ ላይ የሚሰሩ ባለሙያዎች በህጻናት አያያዝ እና በማቆያው ውስጥ መደረግ ስለለባቸው ክትትል እና እንክብካቤ ዙሪያ የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ለማድረግ መሆኑን ገልጸዋል።

ስራ አስፈጻሚዋ አያይዘውም ዩኒቨርሲቲው ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ የህጻናት ማቆያ ማዕከል በመክፈት አሁን ላይ የህጻናት ነርስን ጨምሮ ባለሙያዎችን በማሟላት 80 ህጻናትን በማቆየት ለዩኒቨርሲቲው ሴት መምህራንና ሰራተኞች ስራቸውን በአግባቡ እንዲሰሩ እና ከሌሎች ተጨማሪ ወጭዎች እና እንግልት ማስቀረቱን ገልጸዋል፡፡

በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የቅድመ ልጅነት እንክብካቤ ትምህርት ትምህርት ክፍል መምህር የሆኑት ጥሩየ አብዲ ስልጠናውን ሰጥተዋል።

ስልጠናው ባለፉት ሁለት ቀናት ሲሠጥ ቆይቶ ዛሬ ተጠናቋል፡፡

ጥቅምት10/2017 ዓ.ም

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ