Month: September 2024

በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በአፕል ችግኝ ልማት ዙሪያ ስልጠና መሰጠት ተጀመረ

በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ በግብርና፣ ምግብና ዓየር ንብረት ኮሌጅ አማካኝነት ለዩኒቨርሲቲው አትክልተኞች በአፕል ልማት ዙሪያ የንድፈ ሀሳብና የተግባር ስልጠና መሰጠት ተጀምሯል። በዩኒቨርሲቲው ሆርቲካልቸር መምህርና የስልጠናው አስተባባሪ የሆኑት አቶ አዲሱ ሙሉቀን በግቢው ውስጥ ከ3ሺ በላይ የደጋ አፕል ችግኞች መተከላቸውን አስታውሰው ችግኞችን ለሚንከባከቡ አትክልተኞች ስለ አፕል አመራረት ዝርያና መረጣ፣ ቅጥያ ማስወገድን፣ መገረዝና በሽታ መከላከልን፣ ቀለበት የመስራትን ጠቀሜታ፣ […]

Read More

የማህፀን ጫፍ ቅድመ ካንሰር ምርመራ ዘመቻ ተጀመረ

በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለሁለተኛ ዙር የተካሄደው የማህፀን ጫፍ ቅድመ ካንሰር የግንዛቤ ፈጠራ እና የምርመራ ዘመቻ ተጀምሯል፡፡ የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የተከታታይ ሙያ ማጎልበቻ ማዕከል(CPD)አስተባባሪ ወ/ሮ የውብምርት ሻረው(ረዳት ፕሮፊሰር) ከነሐሴ 21/2016 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለተኛ ዙር የማህፀን ጫፍ ቅድመ ካንሰር የግንዛቤ ፈጠራ ሲሰጥ መቆየቱን ጠቅሰው ከእንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል ጋር በመተባበር የምርመራ ዘመቻ መጀመሩን ገልጸዋል፡፡ አክለውም […]

Read More

በአማራ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም በዚገም ወረዳ ለሚገኙ ተፈናቃዬች የምግብ ድጋፍ አደረገ

በአማራ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም በአዊ ብሄረሰብ አስተዳዳር ዚገም ወረዳ በጸጥታ ችግር ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች 121 ኩንታል በቆሎ የምግብ ድጋፍ አድርጓል፡፡ የፎረሙ ዋና ጸሐፊ ታፈረ መላኩ(ዶ/ር) በአማራ ክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች የተቋቋመው ፎረም የማህበረሰቡን ችግር ከመፍታት አንጻር የጋራ ጥናትና ምርምር ከማድረግ ባሻገር በክልሉ በተለያዩ ጊዜያት በሰው ሰራሽ እና ተፈጥሯዊ አደጋዎች ምክንያት ለሚከሰቱ ችግሮች ምላሽ በመስጠት የተለያዩ […]

Read More

በእንጅባራ ዩኒቪርሲቲ የእንሰሳት እርባታ ማዕከል የልምድ ልውውጥ ተካሄደ

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ የውጭ ዝርያ ያላቸውን የወተት ላሞች በመግዛት ማርባት የጀመረ ሲሆን በማዕከሉ የሚመረተውን ወተት በተመጣጣኝ ዋጋ በዋናነት ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ እያቀረበ ይገኛል፡፡ማዕከሉ ዘመናዊ የእንስሳት እርባታ ዘዴን በመጠቀም የወተት ከብቶችን እያረባ እንደመሆኑ መጠን በአካባቢው በወተት ልማት ላይ ለተሰማሩ የእንስሳት አርቢዎች ተሞክሮውን የማካፈል ሥራ ተከናውኗል፡፡ የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ክንዴ ብርሃን (ዶ/ር) […]

Read More