IU possition

የመካከለኛ አመራር ውድድር ማስታወቂያ
ለእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ማህበረሰብ በሙሉ፡

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የከፍተኛ ትምህርት አዋጅ 650/2001 መሰረት በማድረግ የመካከለኛናመሰረታዊ አመራር ምርጫና አሰያየም መመሪያ አውጥቶ ወደ ስራ ገብቷል፡፡ ይህንን መመሪያ መሰረት በማድረግ በሚከተሉት የኃላፊነት ክፍት ቦታዎች ከአካዳሚክ ማህበረሰብ መካካል አወዳድሮ መመደብ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም፡
1. የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር
2. የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር
3. የአካዳሚክ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር
4. የ1ኛ ዓመት ተማሪዎች አስተባባሪ
5. ተባባሪ ሬጅስተራር
6. የተከታታይ ትምህርት አስተባባሪ
የኃላፊነት ቦታዎች መስፈርቱን የምታሟሉ አመለካቾች ከ08/01/2012 እስከ 14/01/2012 ዓ/ም
1. አሁን ያሉበትን ማዕረግ የሚገልፅ የትምህርት ደረጃ
2. የስራ ልምድ (በኃላፊነት ከሰሩ ይህንኑን የሚገልፅ)
3. የሁለት ተከታታይ ሴሜስተር የስራ አፈፃፃም ግምገማ ውጤት ሰነዶች በማሟሟላት ዘወትር በስራ ሰዓት በተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ወይም ግብርና፣ ምግብና አየር ንብረት ሳይንስ ኮሌጅ ህናፃ ቢሮ ቁጥር 307 ወይም 309 በአካል በመቅረብ ወይም በ email; desalewfentie85@gmail.com መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ማሳሰቢያ
ዋና ዋና ተግባራትን ለማስፈፀም የሚያስችል ንድፈ-ሃሳብ (ስትራቴጂክ ዕቅድ) በውድድሩ ወቅት ማቅረብ አስፈላጊ መሆኑን በመገንዘብ ከወዲሁ እንድታዘጋጁ እየገለፅን ለስትራቴጂክ እቅድ ዝግጅት እንዲያመችና የተወዳዳሪዎችን ዕድል ላለማጥበብ ሲባል አንድ ተወዳዳሪ በመረጡት አንድ ክፍት መደብ ላይ ብቻ መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

መልማይ ኮሚቴው