ለትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

ማስታወቂያ
ለኤክስቴንሽን ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በ2012 የትምህርት ዘመን በቅዳሜና ዕሁድ(weekend Extension) መርሃ-ግብር በመጀመሪያ ዲግሪ አዲስ አመልካቾችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡ስለሆነም መስፈርቱን የምታሟሉ አምልካቾች ከመስከረም26 እስከ ጥቅምት 10/2012 ዓ.ም ድረስ ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፤ ዩኒቨርሲቲው የሚሰጣቸውን የስልጠና መስኮች እና የመግቢያ መስፈርቶችን ዝርዝር እንደሚከተለው አስቀምጠናል፡፡
1. ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ
ማኔጅመንት
ኢኮኖሚክስ
ማርኬቲንግ ማኔጅመንት
ሆቴል ማኔጅመንት
አካዉንቲንግ እና ፋይናንስ
3. ማህበራዊና ስነ-ሰብ ሳይንስ ኮሌጅ
እንግሊዘኛ ቋንቋና ስነ-ፅሁፍ
የኢትዮጲያ ቋንቋዎችና ስነ-ፅሁፍ-
አማርኛ
ጂኦግራፊና አካባቢ ጥናት
ስነ-ዜጋና ስነ-ምግባር ጥናት
ሳይኮሎጅ
ታሪክና ቅርስ አስተዳደር
በልዩ ፍላጎት
EDPM
ህግ(Law)
የቅድመ-መደበኛ ህፃናት
ትምህርት(Early Child Education)
2. ተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ
በኮምፒዉተር ሳይንስ እና በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ (IT)
ሂሳብ
ባይሎጂ
ፊዚክስ
ኬሚስትሪ
ስታቲስቲክስ
ስፖርት ሳይንስ
4. ግብርና ምግብና አየር ንብረት ሳይንስ ኮሌጅ ስር
ደንና አየር ንብረት ሳይንስ
ግብርና ምጣኔ ሀብት
አትክልትና ፍራፍሬ
ተፈጥሮ ሀብት አያያዝ
እንስሳት ሳይንስ
እፅዋት ሳይንስ
የማመልከቻ መስፈርት፡- በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ መስፈርት መሰረት፣ ይኸዉም፡-
1) በአዲሱ የትምህርት ፖሊሲ የመሰናዶ ትምህርት ያጠናቀቀ/ች እና የዓመቱን የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ያስመዘገበ/ች፡፡
2) እውቅና ካለው ኮሌጅ 12+2፣,10+3 ዲፕሎማና 12+3 አድቫንስ ዲፕሎማ አጠናቀው 2፡00 ነጥብ እና በላይ ያላቸው፡፡
3) በቴክኒክና ሙያ ደረጃ-4 ዲፕሎማ ያለዉ/ያላት እና የደረጃ-4 የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል/ትችል
4) ዲግሪ ኖሯቸዉ ሌላ ዲግሪ መማር የሚፈልጉ አመልካቾች የመጀመሪያ ዲግሪ ማስረጃና ኦፊሽያል ትራሰክርቢት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
5) አመልካቾች ለማመልከት ሲመጡ ከ8ኛ ክፍል ጀምሮ ያሉትን ሁሉንም የትምህርት ማስረጃዎች ዋናዉንና አንድ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ለወጣላቸዉ ሁሉም የትምህርት መስኮች ደረጃ-4 የሙያ ብቃት ማረጋገጫ (COC) ተያይዞ መቅረብ ይጠበቅበታል፡፡ መምህራንና የግብርና ባለሙያ አመልካቾች ለመማር የሚፈቀድላቸዉ ዲፕሎማ በተማሩበት የትምህርት ዘርፍ ብቻ መሆኑን እንገልጻልን፡፡
አመልካቾች ለማመልከቻ 50 ብር በዩኒቨርሲቲዉ የባንክ ቁጥር [ኢትዮጲያ ንግድ]-1000258464428 ከፍለዉ ደረሰኝ ይዘዉ መቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
ማመልከቻው የሚከናወንበት ቦታ፡- በዩኒቨርስቲዉ ሬጅስትራር ጽ/ቤት [ሕንጻ ቁጥር-5 G+1 መማሪያ ክፍል 009] ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ባሉት ቀናት፡፡
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የተከታታይና ርቀት ትምህርት ዳይሬክቶሬት