Addis Ababa Case Enforcement Office

የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የአዲስ አበባ ጉዳይ ማስፈጻሚያ ጽ/ቤት የዩኒቨርሲቲውን ሥራዎችና ጉዳዮች በተሻለ መንገድ ለማቀላጠፍ እንዲቻል የተቋቋመ ዘርፍ ነው፡፡ ጽ/ቤቱ በዋናነት የሚከተሉትን ጉዳዮች ያከናውናል፡፡

  1. ከዩኒቨርሲቲው የሚመጡትን የበጀት ጥያቄዎች፣ ውጤቶችና ሪፖርቶች አደራጅቶ ለገንዘብ ሚኒስቴር ተገቢ ክፍሎች ያደርሳል፤ ውጤቱንም ተከታትሎ ለጽ/ቤቱ ያቀርባል፡፡
  2. የሚካሄዱ የግዥ፣ የተሽከርካሪ ጥገና እና እድሳት ሥራን ያስተባብራል፤
  3. ለዩኒቨርሲቲው ከውጭ ሀገር የሚገቡ እንዲሁም ከዩኒቨርሲቲው ወደወጭ ሀገር የሚላኩ ዕቃዎችን ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ተቋማት ድረስ በመሄድ ያስፈጽማል፤
  4. ዩኒቨርሲቲውን የሚመለከቱ አስተዳደር ጉዳዬችን ይከታተላል፤
  5. ከዋናው ግቢ ከሁሉም የሥራ ክፍሎች የሚሰጡ ተግባራት በመቀበል ተፈጻሚ ያደርጋል፤

Biniam Atirsaw
Coordinator
Mobile 091 396 7604

Email:-