Download Image
Download PDF Download Image
Download Image
ማስታወቂያ፦
የመግቢያ ጊዜ የተራዘመ መሆኑን ስለማሳወቅ
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ 4ኛ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች የምዝገባ ፕሮግራም መስከረም 29 እና30/2017 ዓ.ም መሆኑ ቀደም ሲል ተገልጾ የነበረ ቢሆንም የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ባለመጠናቀቃቸው የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 14 እና 15/2017 ዓ.ም መሆኑን እናሳውቃለን።
የጥሪ ማስታወቅያ
ለእንጅባራ ዩንቨርሲቲ አዲስና ነባር የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች በሙኑ፡-
- 4ኛ ዓመት ተማሪዎች የመግብያ ጊዜ ከመስከረም 29-30/2017 ዓ.ም
- 3ኛ ዓመት ፤2ኛ አመት፤1ኛ አመት፤2017 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር አዲስ የተመደባችሁ እና በ2016 ዓ.ም ሬሚዲያል ትምህርት ወስዳችሁ ማለፍያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች መግብያ ጊዜ ጥቅምት 14-15/2017 ዓ.ም መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ማሳሰብያ፡-
አዲስ ገቢ ተማሪዎች ለምዝገባ ስትመጡ ብርድ ልብስ፤አንሶላ፤የትራስ ልብስ፤የስፖርት ትጥቅ፤8ኛ ክፍል ካርድ፤ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክብሪት እና የ12ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውንና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ እንዲሁም 3*4 የሆነ 4 ጉርድ ፎቶግራፍ መያዝ ይጠበቅባችኃ፡፡
እንጅባራ ዩንቨርሲቲ
ማስታወቂያ
ለኤክስቴንሽን ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ
እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በቅዳሜና እሁድ (Weekend Extension) መርሃ-ግብር በመጀመሪያ ዲግሪ አዲስ አመልካቾችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች ከመስከረም 08 እስከ 18 / 2017 ዓ.ም ባሉት ቀናት ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን ዩኒቨርሲቲው የሚሰጣቸው የስልጠና መስኮች እና የመግቢያ መስፈርቶች ዝርዝር እንደሚከተለው ተገልጸዋል፡፡
Institute of Agaw Studies (IAS) is pleased to announce and invite researchers to submit Full Length original research papers for its upcoming Cultural Forum, which will be held in Injibara University in 2017 E.C.