Office of the Registrar

የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ሥራውን ሲጀምር የሬጅስትራር አገልግሎትም ማንዋል በሆነ መንገድ ነበር ሲሰራ የነበረው፡፡ በወቅቱ የሬጅስትራር ሥራ የተጀመረው በአቶ አመነ አፈወርቅ አማካኝነት ሲሆን በሥሩ 4 ያክል ሠራኞች ነበሩት፡፡ በአሁኑ ሰዓት በዋና ሬጅስትራር ጽ/ቤት በአቶ ይመር ቸኮል ዳይሬክተርነት 22 ያክል ሰራተኞችን በውስጡ በመያዝ የተማሪ ምዝገባ ማካሄድ፣ ውጤት ማደራጀት እና ሲመረቁ የምስክር ወረቀት መስጠት የክፍሉ ዋና ዋና ተግባራት ሲሆኑ ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ የሬጅስተራር ሲስተም እንደ ቤተ መጽሐፍት ዲጂታላይዝ ማድረግ ተችሏል፡፡ አሁን ተማሪዎች የሚመዘገቡት፣መምህራንም ውጤት የሚያስገቡበት እንዲሁም የተማሪዎች የመኝታ ክፍላቸውን እና የትምህርት ክፍል ምርጫ ምደባ የሚሰራው በዚሁ ቴክኖሎጂ ነው፡፡ ይህም “SIMS” (Student Information Management System) የሚባል ቴክኖሎጂ ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተገኘ ሲሆን የሬጂስትራርን ሥራን ዘመናዊና የተቀላጠፈ አድርጎታል፡፡  በተጨማሪም የተማሪዎችን መታወቂያን ድጅታላይዝ በማድረግ የአንድ ካርድ ስርዓትን (One Card System) በመዘርጋት ውጤታማ ሥራን ማከናወን ተችሏል፡፡ 

Yimer Chekol

Director, Registrar and Alumni

Mobile +251 90 986 5449

Email:- chekol.yimer@gmail.com