እንጅባራ ዩኒቨርስቲ እና ሌሎች በአማራ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ከክልሉ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ጋር በጋራ ለመስራት የጋራ ስምምነት ተፈራረሙ ።

መጋቢት 22/2018 ዓ/ም እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ

ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 እውን ለማድረግ እና አጠቃላይ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን ለማዘመን እና የደንበኞችን ፍላጎት ለማርካት በዛሬው ዕለት በዩኒቨርሲቲዎች እና በአማራ ክልል ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ቢሮ መካከል በባህር ዳር ከተማ የተካሄደው ስምምነት ወሳኝ መሆኑን የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጋርዳቸው ወርቁ ገልጸዋል።

በስምምነት ፊርማ ስነ-ስራዓት የተገኙት ጋርዳቸው ወርቁ (ዶ.ር) ስምምነቱ በጋራ የምንሠራቸውን ተግባራት ለመለየት እና ለማልማት፣ ድግግሞሽን ለማስቀረት እና ሀብትን በቁጠባ ለመጠቀም ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

በመርሐ ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የአማራ ክልል ሥራ እና ክህሎት ቢሮ ኀላፊ ስቡህ ገበያው(ዶ.ር) ስምምነቱ በክልሉ የእውቀት እና የቴክኖሎጅ ሽግግር አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ስትራቴጅካዊ ስምምነት ነው ብለዋል።

የአማራ ክልል ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጅ ቢሮ ምክትል ኀላፊ የቻለ ይግዘው ቢሮው እንደገና ከተቋቋመ በኋላ ሰፊ ሥራ እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጸው በክልሉ ያለውን የቴክኖሎጅ ዕውቀት እና ሽግግርን ለማሳደግ በትብብር መሥራት ያስፈልጋል ብለዋል። በቀጣይ 5 አመት የክልሉን እድገት በቴክኖሎጂ የታገዘ ለማድረግ ማቀዱን የገለጽት አቶ የቻለ እቅዱን ለማሳካትም ከዩኒቨርሲቲዎች እና ከአጋር አካላት ጋር በትብብር እና በቅንጅት እንደሚሰራ

ያለህን እምቅ አቅም ለይተህ ተጠቀም!!