በ PhD in Education የ3ኛ ዲግሪ(PhD) ለመክፈት የውጭ ሥርዓተ-ትምህርት ግምገማ (External validation workshop) ተካሄደ፡፡

የካቲት 5/2018 ዓ.ም፤እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት እና ስነ ባህሪ ኮሌጅ PhD in Education የ3ተኛ ዲግሪ (PhD) ለማስጀመር የሥርዓተ-ትምህርት ግምገማ የውጭ ግምገማ (External Validation Workshop)ተካሂዷል፡፡
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ  አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝደንት አዕምሮ ታደሰ(ዶ/ር) እንደገለጹት አያይዘውም ዩኒቨርሲቲው መደበኛ የመማር ማስተማር ሥራውን ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የትምህር ፕሮግራሞችን እያስፋፋ በመምጣት በቅድመ ምረቃ 59 ፕሮግራሞች፣ በድህረ ምረቃም 60 ፕሮግራሞች(5 የ3ኛ ዲግሪ(PhD) ) ፕሮግራሞች ተማሪዎችን በመቀበል እያስተማረ  መሆኑን ጠቅሰው ዛሬ የውጭ ግምገማ ከተካሄደው PhD in Education በተጨማሪ በሌሎችም በድህረ ምረቃ ፕሮግራም ለመክፈት ሂደት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል ፡፡
  ዶ/ር አዕምሮ አያይዘውም PhD in Education መክፈት አስፈላጊነት አስመልክቶ የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት መሠራቱንና በየደረጃው  ከትምህርት ክፍል ጀምሮ እሰከ ኮሌጅ የውስጥ ግምገማውን አጠናቅቆ በዛሬው ዕለት  በታዋቂ የዩኒቨርሲቲ ምሁራን የውጭ ግምገማ በቨርችዋል መካሄዱን ገልፀዋል፡፡