የካቲት 05/2018 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
ከሀገራችንና ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ወደ ዩኒቨርሲቲው የተቀላቀሉ አዲስ ተማሪዎች ከእንጅባራ ከተማ ነዋሪዎች ጋር በቃል ኪዳን ትስስር የሚፈጥሩበት ዝግጅት በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ‘‘አዲናስ የተማሪ ቤተሰብ የቃል ኪዳን ትስስር ”ፕሮግራም በዛሬው እለት የተማሪ ቤተሰብ ትስስር መርሃግር ተካሂዷል፡፡
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ጋርዳቸው ወርቁ (ዶ/ር) ‘‘ አዲናስ የተማሪ -የቤተሰብ ትስስር” ዓላማ ወደ ዩኒቨርሲቲው የሚቀላቀሉ ተማሪዎች በፍቅርና ቤተሰባዊነት እንዲታቀፉ ማድረግ መሆኑን ተናግረው የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲም የተማሪ-ቤተሰብ የቃል-ኪዳን ትስስር ፕሮጀክትን “አዲናስ” ብለው መሰየማቸውንም ገልፀዋል።
ዶ/ር ጋርዳቸው አያይዘውም ለስያውሜው የተሰጠው ቃል በአገውኛ ቋንቋ “አዲናስ” ማለት በዋናነት ትልቅ እንግዳ ሲመጣ የምንጠቀመው “እንኳን በደህና መጡ (welcome) ማለት መሆኑን ጠቅሰው ለትስስር ፕሮጀክቱ የማህበረሰቡን እሴት የጠበቀ ስያሜ መሆኑን ተናግረዋል።
ዶ/ር ጋርዳቸው አያዘውምም ከአዲናስ ቃል ኪዳን ፕሮጀክት በአጭር ጊዜ ሚጠበቅ ውጤት ተማሪዎች ለአካባቢው ባዳ እና ባይተዋር እንዳይሆኑ፣ ብቸኝነት እንዳይሰማቸው፣ በቅርበት ተማሪዎች ለሚገጥማቸው ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግር እንደወላጅ በመምከር፣ በማገዝ፣ በመገሰጽ እና ተማሪዎችን በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው ውጤታማ ማድረግ መሆኑን ገልጸዋል፡፡


