የመጀመሪያው ዓለማቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ በስኬት ተጠናቀቀ፡፡
ግንቦት 09/2018 ዓ.ም፣ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፣ የሳይበር ደህንነት እና ዲጂታል ኢኮኖሚ (Artificial Intelligence, Cyber Security and Digital Economy) በሚሉ ርዕሰ-ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ የተለያዩ ሀገራት ምሁራንን ያሳተፈው የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ በስኬት ተጠናቋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ጋርዳቸው ወርቁ በኮንፈረንሱ የማጠቃለያ መርሃ ግብር ንግግራቸው የትምህርት ሥርዓታችን ዲጂታላይዝድ በሆነ የኢንዱስትሪ ሥነ ምህዳር የሚመራ እና የዲጂታል ቅልጥፍና ያላቸው ተመራቂዎችን ለማፍራት በትኩረት መሰራት እንዳለበት ተናግረዋል።
በምርምር ኮንፈረንሱ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ተመራማሪ ምሁራን የምርምር ሥራዎቻቸውን በኦንላይንና በአካል ተገኝተው (Online & Face-to-Face) ለተሳታፊዎች ያቀረቡ ሲሆን ከጥናታዊ ጽሑፍ አቅራቢዎች መካከል ኬንያዊቷ ተመራማሪ ቴሬሳ ነጀሪ በአካል በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ተገኝተው የምርም ሥራዎቻቸውን ካቀረቡት የውጭ ሀገራት ምሁራን መካከል አንዷ ናቸው፡፡
ተመራማሪዋ ጥናታዊ ጽሁፋቸውን ለተሳታፊዎች ካቀረቡ በኋላም ለሆቴልና ቱሪዝም ትምህርት ክፍል ተማሪዎች የማነቃቂያ ንግግር (Motivational Speech) በማድረግ የህይወት ተሞክሯቸውን አካፍለዋል፡፡
በመጨረሻም ለሁሉም ጥናታዊ ጽሑፍ አቅራቢዎች የምስጋና ሰርተፊኬት ተበርክቶላቸው ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የፕሮግራሙ ተሳተፊዎች በዩኒቨርሲቲው ኤግዚቢሽን ማዕከል ጉብኝት አድርገው ኮንፈረንሱ በስኬት ተጠናቋል፡፡
ያለህን እምቅ አቅም ለይተህ ተጠቀም!








